The new face of Banking is here!

አክፋይ!

አክፋይ ለምን?
አክፋይ እንደ ኢትዮጵያዊ ልማድ የትንሳኤውን ብርሃን ከወዳጅ ዘመድ ጋር የሚካፈሉበት ልዩ የፋሲካ ስጦታ ነው፡፡ መክሊት ግብረ ሰናይ ማህበርም ከአሐዱ ባንክ ጋር በመተባበር የአንድ ወጣትን ህይወት በመለወጥ የትንሳኤውን ብርሃን እንዲካፈሉ ከአብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርሔር እስከ ዳግመ ትንሳኤ የሚቆይ የአክፋይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አዘጋጅተውሎታል፡፡

 

አክፋይ ለማን?
ስራ አጥነትና የመነሻ ካፒታል ዕጥረት የሀገራችን ወጣቶችን በተለይም ኦርቶዶክሳውያንን የሚፈታተን ተግዳሮት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንንና ሌሎች የወጣቶችን ችግሮች ለመቅረፍ የተነሳው የመክሊት ግብረ ሰናይ ማህበር ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ጭምር መትረፍ የሚያስችላቸው የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ከአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር የሚተሳሰሩበትንና ሥራ ለመጀመር የሚችሉበትን ዝቅተኛ መነሻ ካፒታል ከነጻ ስልጠና ጋር ለማቅረብ ‹‹ ገብርኄር ፕሮጀክት›› የተሰኘ ፕሮጀክት ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
በፕሮጀክቱ ለአንድ ሰው የብድር ትስስርና ሥራ ማስጀመሪያ ዝቅተኛ ገንዘብ ተብሎ የተመነው 27,800 ብር ($490 USD) ሲሆን በዚህ የአክፋይ የድጋፍ ማሰባሰቢያ 20 ልጆችን ተጠቃሚ ለማድረግ በማቀድ ብር 556,000 ($10000 USD) ለመሰብስብ ግብ አስቀምጧል፡፡

 

አክፋይ እንዴት?
በአክፋይ የብርሃነ ትንሳኤውን ደስታ ከወጣቶቹ ጋር ለመካፈል ከፈለጉ ከስር በሚገኙ የቻፓ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ሊንኮችን በመጠቀም ወይም በአሐዱ ባንክ የአሐዱ በረከት ገጽ በመጠቀም ከፔይፓል፣ቴሌ ብር፣ ኤምፔሳ፣ኢ ብር ወይም ከባንክ አካውንቶ ያሻዎትን ገንዘብ መለገስ ይችላሉ፡፡

መልካም የትንሳኤ በዓል