faq Esubalew D August 2, 2023

FAQ Descriptions
For Your Convenience!

AHADU BANK

FAQ Descriptions
For Your Convenience!

FAQ’s

አዲስ አክሲዮን ከሐምሌ 9 2015 ጀምሮ ሽያጭ ይጀመራል፡፡እስከዛው ግን በአቅራቢያ በሚገኝ የአሐዱ ባንክ ቅርንጫፍ በመቅረብ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት መመዝገብ ይቻላል።
ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ለሆኑ ባለአክሲዮኖች ከብር 20,000 ጀምሮ ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆነው የውጪ ዜጋ ለሆኑ ከብር 50,000 ብር ጀምሮ መግዛት የሚቻል ሲሆን ከፍተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን ብር 99,999,500 ድረስ ይሆናል።
ነባር ባለአክሲዮኖች ተጨማሪ አክሲዮን ሲገዙ ምንም አይነት የአገልግሎት ክፍያ አይከፍሉም።
ባንኩ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቶ ከሐምሌ 9 2014 ጀምሮ ስራ የጀመረ ሲሆን ለደንበኞቹ ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን እንዲያስችለው ቅርንጫፎቹን በመላው ሃገሪቱ በማስፋፋት ላይ የሚገኝና በአሁን ወቅትም የቅርንጫፎቹን ብዛት ወደ 70 ማድረስ ችሏል ፡፡ በመሆኑም ባለአክሲዮኖች ተጫማሪ አክሲዮን በመግዛትና ሂሳብ በመክፍት የባንኩን እድገት በበለጠ እንዲያፋጥኑ ጥሪ እያቀረብን ባንኩ የደርሰበትን ደረጃ ለማየትና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዋናው መ/ቤት ፍላሚንጎ ሰንሻይን ህንጻ ወይም በአቅራቢዎ በሚገኙ ቅርንጫፎች በመገኘት እንዲጎበኙ ጥሪ እናቀርባለን ።
በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም መገኘት ለሚችል ሰው ውክልና በመስጠት ግዥውን መፈጸም ይቻላል፡፡