አሐዱ ባንክ ለአዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አቀባበል አደረገ! Esubalew D March 14, 2024

አሐዱ ባንክ ለአዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አቀባበል አደረገ!

አሐዱ ባንክ አክሲዮን ማህበር በ2ኛ መደበኛ ጠቅላላ የባለአክሲዮኖች ጉባዔ የተመረጡትን አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አቀባበልና የሥራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት አከናወነ። በዕለቱ የባንኩ የመጀመሪያ ቦርድ በመሆን ያገለገሉ አባላት በክብር የተሸኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸው የፀደቀ 12 አባላት ያለው አዲሱ ቦርድም  ከአሁን ቀደም በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢነት እና በምክትል ሰብሳቢነት ያገለገሉትን አቶ አንተነህ ሰብስቤን  እና አቶ መኰንን ሰሙን በድጋሜ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ እንዲሆኑ መርጦ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጽ/ቤትን ሰይሟል። ቦርዱ ከባለአክሲዮኖች የተጣለበትን ከፍተኛ አደራ ለመወጣት በቁርጠኝነት እንደሚሠራም ገልጿል።

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!
Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *