አሐዱ፡ባንክ እንዛመድ ብሎ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ጀመረ! Esubalew D March 6, 2024

አሐዱ፡ባንክ እንዛመድ ብሎ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ጀመረ!

#እንዛመድ/ #Let’s_Relate
አሐዱ፡ባንክ ከብዙዎች ለብዙዎች በሚል መርሕ ከብዙኃኑ ጋር ለመዛመድ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ የካቲት 18/2016 ዓ.ም በይፋ ጀመረ፡፡ ከኪነ-ጥበብ እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የጀመረውን ዝምድና መሠረት በማድረግ ለቀጣይ ሦስት ወራት የሚቆይ ንቅናቄ የጀመረው አሐዱ፡ባንክ፤ በተልዕኮው ላይ በግልፅ እንዳሰፈረው ዘመኑን በዋጀ የባንክ አገልግሎት በመስጠት በኢትዮጵያውያን/ት የምጣኔ ሀብት እድገት ላይ አሻራ እንደሚያሳረፍ ያምናል፡፡ አሐዱ፡ባንክ ሰብአዊነትን ወይንም ሰውነትን ማዕከል ባደረጉ አገልግሎቶቹ ከብዙዎች ጋር እንደሚዛመድ እና ዘመድ (#እንዛመድ / #Let’s_Relate) እንደሚሆን እየሔደ ካለበት እና ወደፊት ሊሔድበት ካለመው አቅጣጫ በመነሣት መናገር ይቻላል፡፡ ይህ ዝምድና እና ቤተሰብ ወዳድነት ደግሞ የሚወለደው እና የሚጎለምሰው የአሐዱ፡ባንክ ቤተሰብ ቁጥር ሲያድግ፤ የባንክ ባለቤት የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ሲጨምር እንደሆነ የሚያምነው አሐዱ፡ባንክ ዛሬውኑ የአሐዱ ቤተሰብ እንዲሆኑ ይጋብዛል፡፡አክሲዮን ይግዙ፤ አካውንት ይክፈቱ፤ የባንኩን የማኅበራዊ ገጾች ላይክ፣ ሼር እና ሰብስክራይብ፤ በማድረግ ዝምድናን ይፍጠሩ፡፡ #እንዛመድ / #Let’s_Relate ንቅናቄውን ይቀላቀሉ፡፡
Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *