አሐዱ፡ባንክ ለኪነ-ጥበብ፤ኪነ-ጥበብ ለአሐዱ፡ባንክ Esubalew D January 24, 2024

አሐዱ፡ባንክ ለኪነ-ጥበብ፤ኪነ-ጥበብ ለአሐዱ፡ባንክ

ማክሰኞ ጥር 14/2016 ዓ.ም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣የቦርድ አባላት፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ሌሎች የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት አሐዱ፡ባንክ ለኪነ-ጥበብ፤ኪነ-ጥበብ ለአሐዱ፡ባንክ በሚል መሪ ቃል ከታዋቂ እና ተወዳጅ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በማርዮት ኤክስኪዩቲቭ አፓርትመንት ሆቴል ስኬታማ የውይይት መርሐ ግብር ተካሔደ። በመርሐ ግብሩም ስለ ባንካችን ተልዕኮ፥ራዕይ ፥ ዕሴቶች እና ስለ ተቋቋመበት ዓላማ እንዲሁም አሐዱ፡ባንክ የኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ላይ ይዟቸው ስለሚመጣቸው የፋይናንስ አገልግሎቶች እንዲሁም ኪነ-ጥበቡ ለአሐዱ፡ባንክ ስለሚያበረክተው አስተዋፅኦ ሰፊ ትንታኔ ተሰጥቷል። አሐዱ፡ባንክ የብዙዎች ለሆኑት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች “ከብዙዎች ለብዙዎች” ብሎ በተነሣው መርሑ በአጋርነት አብሮ ለመሥራት በመወሰኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። በዚህ ውጤታማ በነበረው ኩነት ላይ በቀረቡት ገለፃዎች እና በአሐዱ፡ባንክ ቀጣይ ጉዞ ዙሪያ ጥያቄ እና አስተያየቶች ከኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተሰንዝረው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹም አሐዱ፡ባንክ የተቋቋመበትን ዓላማ በመደገፍ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን በአፅንኦት አስረድተዋል፡፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *