በኪነ-ጥበቡ የተጀመረው አብሮነት ከጋዜጠኞችም ጋር ቀጥሏል Esubalew D February 9, 2024

በኪነ-ጥበቡ የተጀመረው አብሮነት ከጋዜጠኞችም ጋር ቀጥሏል

ባንካችን ሰኞ ጥር 27/2016 ዓ.ም  የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣የቦርድ አባላት እና ሌሎች የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት  ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በማርዮት ኤክስኪዩቲቭ አፓርትመንት ሆቴል ስኬታማ የውይይት መርሐ ግብር አካሒዷል። በመርሐ ግብሩም ስለ ባንካችን ተልዕኮ፥ራዕይ ፥ ዕሴቶች እና በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ስላከናወናቸው ተግባራት፣አሁን እየሠራቸው ስላሉ ኢትዮጵያዊነትን ያነገቡ አንኳር ጉዳዮች፣ አሐዱ፡ባንክ ለዘርፉ  ይዞ ስለመጣው የፋይናንስ አገልግሎቶች እንዲሁም  አሐዱ፡ባንክ ለኢንዱስትሪው ስለሚያበረክተው አስተዋፅኦ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል። በዚህ ውጤታማ በነበረው ኩነት ላይ በቀረቡት ገለፃዎች እና ከአሐዱ፡ባንክ ጋር ስለሚኖራቸው ቀጣይ ጉዞ ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ የሚሹ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከባለሙያዎች ተሰንዝረው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ባለሙያዎቹም የአሐዱ፡ባንክን ዓላማ  በመደገፍ በጋራ በመሥራት አብሮ ለማደግ ዝግጁ  መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *